ሆርን ሪቪው:

አምባሳደር በመጀመሪያ ይህንን ቃለመጠይቅ ለማድረግ ጊዜ ስለሰጡን ማመስገን እንፈልጋለን፡፡ ኢትዮጵያ ባለም ላይ ስለምትገኝበት ሁኔታ ይሄንን ያለፈውን ዓመት እንዴት ይገልጹታል?

2021 ኢትዮጵያ ብዙ ውጣ ውረዶች ያለፈችበት ጠመዝማዛ ጉዳዮች አስቸጋሪ ክስተቶች የተከሰቱበትና የፖለቲካ መጠማዘዞች የነበሩበት ዓመት ነበር፡፡ ይህም ኢትዮጵያ የሚታመኑ ወዳጆቿን ከደግ ጊዜ ብቻ ወዳጆቿ ለመለየት ረድቷታል፡፡ ይህ ያለፈው ዓመት የቀጠናችንና ዓለም አቀፍ አጋሮቻችንን ፍላጎቶችና ስሜቶች አሳይቶናል፡፡ በህግ የተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት ላይ የጫና ዘመቻ በማድረግ ወደነርሱ ፍላጎቶች ለማዘመም ሲሞከር በማያሻማ ሁኔታ ተመልክተናል፡፡ እንደማንኛውም አገር ኢትዮጵያም የራሷ የውጪ ጉዳይ ፍላጎቶችና ምርጫዎች ያለው ፖሊሲ ስላላት የውጪ ሀይሎች በፈለጉት ጉዳይና ሀሳብ ሊገዛ አይጠበቅበትም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰሜኑ ከተከሰተው ድህረ ግጭት ጉዳይ ጋር ብቻ ሳይሆን ሉአላዊነቷንና ነጻነቷን በአፍሪቃ ቀንድ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ማዶ ለማረጋገጥ ተጠምደን ቆይተናል፡፡

ሆርን ሪቪው:

የሚገጥሙንን ተግዳሮችና ለማሻሻል ያሉት ክፍተቶች ምንድናቸው?

ዋናው መሰረታዊ ጥያቄ ውስጣዊ ልዩነቶቻችንና አለመስማማታችንን እንዴት መፍታት ችለን ወደፊት መራመድና የብልጽግናን መንገድ መጓዝ እንችላለን የሚለው ነው፡፡ ምንም እንኳን ያሉንን ችግሮች በሙሉ ባንድ ጊዜ መፍታት ባንችልም፤ ነገር ግን በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አገራዊ መግባባት ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ ከሁሉም መጀመሪያ የራሳቸንን የውስጥ ችግሮች ለመፍታት የበለጠ መጣር አለብን፡፡ ያሉብንን ክፍተቶች ለማጥበብ ተጨማሪሥራዎች አሉብን፡፡ በዚህ ረገድ መጪው ሁሉን አቀፍ ውይይት ችግሮቻችንን በበለጠ ለይተን የመረጥነውን ጎዳና ለመከተል በደንብ ይረዳናል፡፡ ኢትዮጵያ ረጅም ያገረ መንግሥት ታሪክ ቢኖራትም ነገር ግን የራሳችንን የውስጥ ችግሮች ከመፍታት መቻል አንጻር ወደ መቶ ዓመት ወደኋላ ቀርተናል፡፡ በዚህ ውጥንቅጡ በወጣ ብዙ የተለያዩ ፍላጎቶች በሚከሰቱበት ዓለም ላይ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማ በመቅረትና በልዩነቶቻችን ውስጥ ሠርገው ገብተው ለጥቃት እንዳንጋለጥ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዱ ኃይል መንግሥትም ሆነ የሚዲያ አካል ወይም ሌላ የራሱ ፍላጎቶች አሉት፡፡ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ከማንም ጋር የቁርባንጋብቻ ስላልፈጸመች ይልቁንም የራሷን ያገርውስጥም ሆነ የውጪ ጉዳይ የፖሊሲ ቅድሚያዎች ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት፡፡ ኢትዮጵያ ምን ጊዜም ቢሆንየገለልተኛ አገሮች ንቅናቄ አካል ስትሆን ይህንን አቋሟን ወደፊትም ትቀጥልበታለች፡፡ ይሄ ደግሞ የራሱ የሆነ ድብቅ ወይም አሳሳች ችግር ሊኖረው ይችላልና ኢትዮጵያ ወዳጆቿን በደንብ ለይታ የወደፊት ያጭር ጊዜና የረጂም ጊዜ ግቦቿን አስቀምጣ ፍላጎቶቿን ማሟላት አለባት፡፡ አለበለዚያ በታላላቅ መርከቦች ፍትጊያውስጥ ተውጣ እንዳትቀር ያሰጋታል::

ሆርን ሪቪው:

ሕግ በሚገዛው ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ ያለን ይመስልዎታል?

ዓለም አቀፍ ልምዶች አሉ፡፡ ደንቦችም በእርግጠኝነት አሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ደንቦች የተቀመጡት ሁሉንም እኩል እንዲያገለግሉ ሳይሆን ይልቁንም ደንቦቹን ያወጡትን ለማገልገል ነው፡፡ ኃይልና ችሎታ አቅም ያላቸው አገሮች አልፎ አልፎ ደንቦቹን ለራሳቸው ፍላጎቶች ሲያውሉ ይሄ ችሎታ የሌላቸው ደግሞ ሲገደዱ እናያለን፡፡ እንደኛ አርል ላለ አዳጊ አገር በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ በደንብ በተጠና እቅድና አገራዊ ፍላጎቶችን በየጊዜው ማጤንና ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር መስተካለል ያስፈልገዋል፡ ፡ ስለዚህ ነው በሕግ በሚገዛ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ ነን ከማለት ወደኋላ የምለው፡፡

HORN REVIEW:

ለመጪው ሁሉን አቀፍ ውይይት የታቀዱት ዋና ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?

በመጀመሪያ ብሔራዊ ውይይት የሚለው ቃል ላይ ጥርት ያለ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ ተጠባቂው ብሔራዊ ውይይት ሊያሳካ የሚፈልገው በሕዝቦች መካከልና በፖለቲካ ልሂቃን የሚጋሩት ግብ መንደፍ ነው፡፡ ሽብርተኛ ተብለው ከተፈረጁ ሃይሎች ጋር ድርድር ለማካሄድ አይደለም፡፡ ይህ ጉዳይ እንዲያልቅ፤ ወራት ምናልባትም ዓመታት ሊፈጅ ይችላል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሕወሀት በእንደዚህ ዓይነቱ ውይይት ለመሳተፍ እቅድ የለውም፤ ምክንያቱም የሚያቀርባቸው ሀሳቦች እርስበርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው፡፡ ማንም ሕጋዊ መንግሥት ከሽብርተኛ ኀይሎች ቅድመ ሁኔታዎች መቀበል አይጠበቅበትምና፡ ኢትዮጵያም በዚህ ጉዳይ ላይ ልትገደድ አትችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታዎችንና ደረጃዎችን በግልጽ ማስቀመጥ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነት ሲሆን ነገሮችን ወደነበሩበት የማስተካከልና የመልሶ ማቋቋም ጥረቶችን ማድረግ አለበት፡፡

ሆርን ሪቪው:

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያሉ የመንግስት ሰራተኞችን ተሻለ ሁኔታ ለማሟላት የሚኒስቴሩ የአቅም ግንባታ እርምጃዎችእ እየተወሰዱ ነው?

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሠራራችንን እና አጠቃላይ ቁመናችንን ለማሻሻል የተለያዩ ለውጦችን እያደረገ ነው። ሚኒስቴሩ ለውጦችን ከማቅረባቸው በፊት በሠራተኞቹ ላይ ረጅም እና ጥልቅ ግምገማ አድርጓል። ባለ ሁለት አቅጣጫ ግምገማችን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖቻችንን በተሻለ ሁኔታ ለመለካት ግላዊ እናደረጃውን የጠበቀ ፈተናን ያካትታል። በአንጋፋ ሠራተኞችና በአንፃራዊነት አዲስ በሆኑ ሠራተኞቻችን መካከል በንድፈ ሃሳባዊ ዕውቀት እና ልምድ ላይ ክፍ ያለ ልዩነት አለ ፣ ልዩነቱ በአብዛኛው በሥራ ላይ ከመቆየት ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው። ከአቅም ግንባታ አንፃር ሚኒስቴሩ ለሠራተኞቻችን የቴክኒክ ዕውቀትና ክህሎትን መሠረት ያደረገ ሥልጠና በመስጠት እነዚህን ክፍተቶች ለማስተካከል ቅድሚያ ሰጥቶ ይሠራል።

2021 ኢትዮጵያ ብዙ ውጣ ውረዶች ያለፈችበት ጠመዝማዛ ጉዳዮች አስቸጋሪ ክስተቶች የተከሰቱበትና የፖለቲካ መጠማዘዞች የነበሩበት ዓመት ነበር፡፡ ይህም ኢትዮጵያ የሚታመኑ ወዳጆቿን ከደግ ጊዜ ብቻ ወዳጆቿ ለመለየት ረድቷታል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት የሥራ ላይ ሥልጠናን ለአቅም ግንባታ እንደ ቀዳሚ መሣሪያ እንጠቀም ነበር :: ይህም የጠቅላላ ዕውቀት ባለቤቶች በብዛት እንዲኖር አድርጓል። በዲፕሎማሲያዊ ሥራችን ላይ ልዩ ትኩረት በሚሰጣቸው አካባቢዎች ፣ ጂኦግራፊያዊ ቦታዎች እና ጭብጥ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ትኩረት በማድረግ ይህንን ክፍተት ለማሟላት አስበናል። በተጨማሪም በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ውስጥ የነበረውን ጊዜ ያለፈበት አሠራር ማለትም እያንዳንዱ ባለሙያ ሠራተኛ ከሶስት አመት አገልግሎት በኋላ አግባብነት ያላቸው ጥናቶች ስለማካሄዱ ወይም የቋንቋዎች ችሎታ ከግምት ውስጥ ሳይገባ አለም አቀፍ ስምሪትየሚረጋገጥበትን ልምድ ለውጠን ፣ በማሻሻል ላይ እንገኛለን። ይህ አሠራር በተወሰነ ርእሰ ጉዳይ ላይ የተካኑ የባለሙያዎች እጥረት እና የጠቅላላ ዕውቀት ባለቤት ሠራተኞች ብዛት እንዲፈጠር አድርጓል።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሕወሀት በእንደዚህ ዓይነቱ ውይይት ለመሳተፍ እቅድ የለውም፤ ምክንያቱም የሚያቀርባቸው ሀሳቦች እርስበርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው፡፡

በተጨማሪም፣ ካስፈላጊው ብዛት በላይ የተሞሉት የውጪ ሚሲዮኖቻችን ያስከተሉት የወጪ ሸክም ይህን አሰራር ለመሻር ሌላው ምክንያት ነው። ለምሳሌ በአንድ አካባቢ ውስጥ ያሉ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ አገሮች ኤምባሲዎች አራት ወይም አምስት ዲፕሎማቶች ሲኖራቸው፣ በዚያው ክልል ያለው የኢትዮጵያ አቻ እስከ 15 ዲፕሎማቶች ሊኖሩት ይችላል። ሚኒስቴሩ በውጭ ፖሊሲያችን ዓላማ መሰረት፡ የሚሲዮኑን ወይም የኤምባሲውን መጠን ለመመዘን ፤እንደ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሁኔታ፣ እንደ የዲያስፖራው ፍላጎቶች፣ የኢንቨስትመንት እና ከአገሮቹ አጋርነት ጋር ባሉ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ትኩረት ለመስጠት ያለመ ነው። ሚኒስቴራችን ተደራሽነቱን ለማስፋት በባህላዊ ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን በዚህ የዲጂታል ዘመን መሳሪያዎችን ለመጠቀም አስቧል። ምንም እንኳን ይህ የታቀደው ማሻሻያ በስርአቱ ላይ ድንጋጤዎች ሊፈጥር ቢችልም፣ የዚህ ማሻሻያ የረዥም ጊዜ ፋይዳዎች እጥፍ ድርብ እንደሚሆኑ አምናለሁ።

ሆርን ሪቪው:

ወደ 2022 ዓም ስንሄድ በሚኒስቴሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሶስት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው?

ዋናዎቹ 3 ጉዳዮቻችንን; አንደኛ የአገር ውስጥ ጉዳዮቻችንን በተገቢው መንገድ አካሂደን ያገራችንን ገጽታ አድምቀን ብቃታችንን አስረግጠን ማሳየት ነው፡፡ ሁለተኛ፣ ሚኒስቴሩ የኢንቨስትመንትና፣ የቱሪዝም ምንጭ እንዲሆኑ፣ በውጭ ሀገራት የሚደረጉ ዘመቻዎችን በመዋጋት ረገድ እገዛ እንዲያደርጉ ፤ከኢትዮጵያውያንና፣ ከትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር አቅዷል። በመጨረሻም፣ የኢኮኖሚ እድገታችንን ለማጎልበት ባገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ማካሄድ እየጀመርን ነው። አላማችን ቀስ በቀስ እራሳችንን መቻል ቢሆንም፣ አሁንም የኢንቨስትመንት ፤ የእርዳታ አጋርነት እና ፕሮጀክቶችን መጠየቃችን ይቀጥላል።

ሆርን ሪቪው:

አሁን ካለው የፖለቲካ አውድ አንፃር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች እንዲሁም በዲያስፖራ አካባቢዎች ትልቅ መነሳሳቶች ታይተዋል። ሚኒስቴሩ በዲጂታሉ ዓለም ላይ እንደዚህ ያሉ የዜጎች ዲፕሎማሲ ጥረቶችን ለማበረታታት እንዴት አቅዷል?

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የህዝብ ግንኙነት ክፍሎችን እያሰፋን እንገኛለን፤ እንዲሁም በዲጂታል ተግባቦት ዘርፍ ከፍተኛ የሰለጠኑ ወጣት ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን። ከሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በተጨማሪ ዲያስፖራውን ወደእኛ ለማቀራረብና ለማዋሃድ የቋንቋ መሰረታችንን ወደ ፈረንሳይኛ፣አረብኛ፣ ስፓኒሽ እና እንግሊዘኛ እያሰፋን ነው። ሌላው፣ ከኢትዮጵያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ከዲያስፖራ ኤጀንሲዎችና ድርጅቶች ጋር ያለንን ትብብርናእንቅስቃሴ ለማሳደግ ዓላማችን ነው።

በዲያስፖራው የሚታየው የመቀራረብና መተሳሰብ ደረጃ የሀገር ውስጥ አንድነታችን ነጸብራቅ ነው። መጪው ሀገር አቀፍ ውይይት በዲያስፖራው ውስጥም የጠበቀ ትስስር ይፈጥራል የሚል ተስፋ አለኝ። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ሚሲዮኖች የዲያስፖራ አባላትን በቀጥታ ለማነጋገር የተለያዩ የኦንላይንሴሚናሮችን፣ ምክክር እና ውይይቶችን በማዘጋጀት ላይ ናቸው። በዲያስፖራ ውስጥ ለመሳተፍ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት አበረታች ነው።

ሆርን ሪቪው

በ 2022 ዓም ምን አዲስ ነገር መጠበቅ እንችላለን?

2022 የዲያስፖራውን ተሳትፎ የበለጠ እንደሚያመጣ ተስፋችን እና እቅዳችን ነው። እየተካሄደ ያለው ታላቁ ወደ ሀገር ቤት መለስ ዲያስፖራው በራሱ መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነታ እንዲገመግም ሰፊ እድል እንደሚፈጥር ተስፋ እናደርጋለን። ባገራቸው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ባለድርሻ አካላትእንደመሆናቸው መጠን ትክክለኛ መረጃን በማሰራጨት ረገድ የዳያስፖራው ሚና ወሳኝ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጦርነቱ ሳቢያ በሆስፒታሎች፣ በትምህርትቤቶችና በመሳሰሉት የህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ከደረሰው ውድመት የተነሳ መልሶ ግንባታውን ለማገዝ ከዲያስፖራው በኩል የሚበረታታ ጥረት አለ። የቀጣዩአመት ዋና ሥራችን የሀገር ውስጥ ተሀድሶ ጥረታችንን በበለጠ ማጠናከር ነው። ይህም አጋሮቻችንን እና ወዳጆቻችንን በዲፕሎማሲያዊ እና በልማት ዘርፎችለበለጠ ትብብር በማበረታታት ረገድ ትልቅ ተጽእኖ ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን። በተጨማሪም፣ ግጭቱን ብናልፍም፣ ለተሻለ ተስፋ፣ የወደሙ መሠረተልማትን እንደገና መገንባት እንጀምራለን። የሚቀጥለው አመት የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራን የምናስተካክልበት አመት ይሆናል፡፡

ሆርን ሪቪው:

ለወጣት ባለሙያዎች በአለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ለዲፕሎማሲ እና ለአለም አቀፍ ጉዳዮች ያላቸውን ፍቅር ለማደስ አሁን ያለ ወይም የወደፊት እቅዶች ይኖሩ ይሆን?

በመጪው አመት በዩንቨርስቲ ካምፓሶች እና አካባቢ በአህጉራችን፣ በቀጠናችን እና በአለም ላይ በተመለከቱ ዋና ዋና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በርካታ ወርክሾፖችን፣ የፓናል ውይይቶችን እና ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት እቅድ ይዘናል። በቀጠናችን ውስጥ ካሉ ሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር, እኛ በዚህ ረገድ በደንብ ዘግይተናል፡፡ ይህ በከፊል ከፋይናንስ አቅርቦት ቁርጠኝነት ማነስ እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ ጥረት ባለመኖሩ ነው፡፡በዚህ ረገድ ብዙ መሥራት የሚጠበቅብን ሲሆን፤ ሚኒስቴራችን አሁን ያለውን የዜጎች የዲፕሎማሲ መነቃቃት በዩኒቨርሲቲዎቻችን ግቢዎች ለማስቀጠል አቅዷል።

Share