አምባሳደር ሞሃሙድ ድሪር ግህዲ ለመጀመሪያ ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆነው ከተመረጡበት ከ1990ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያን በብዙ የፖለቲካ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። በመቀጠልም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ለአራት ተከታታይ ጊዜያት የአምባሳደርነት እና የሚኒስትርነት ቦታዎችን አገልግለዋል። ከዋና ዋናዎቹ የዲፕሎማሲ ስራዎቹ መካከል በግብፅ የስድስት አመት አምባሳደርነት፣ በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል በተካሄደው የሶስትዮሽ GERD ድርድር ውስጥ ያበረከቱት የአማካሪነት ሚና እንዲሁም በ2019 የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት እና የሃይል አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ጋህዲ የሰላም ስምምነትን ለማስፈን ያደረጉት ጥረት ይጠቀሳል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። አምባሳደር ሞሃሙድ ድሪር ግህዲ በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን ውስጥ ኮሚሽነር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ማስተባበያ፡

አምባሳደር ድሪር እነዚህን ጥያቄዎች እየመለሱ ያሉት አሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ውይይት ኮሚሽን ውስጥ ባላቸው ኃላፊነት ሳይሆን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞ ዲፕሎማትነታቸው እና ኢትዮጵያቸ በሱዳን በ2019 በባደረገችው የሽምግልና ጥረት ግንባር ቀደም ተደራዳሪነት ሚናቸው ነው።

ሆርን ሪቪው ፡

ኢትዮጵያ በሱዳን ጄኔራሎች፣ በአካዳሚክ ምሁራንናበኤክስፐርቶች ማህበረሰብ እንዲሁም በህብረተሰቡ መካከልሽምግልና ለማድረግ ያቀረበችበት ምክንያት እና ተስፋ ምን ነበር?

በሕወሃት በኩል ያገረሸው ትንኮሳና ጥቃት በንጹሃን ዜጎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እና ኑሯቸውን እያወከ ነው። መንግስት ለእርዳታ የሚሆን ገንዘብ ቢመድብም ጠላት ቡድኑ ለትግራይ ብቻ ሳይሆን በግጭት ለተጎዱት የአፋር እና የአማራ ክልል ዞኖችም እንዳይደርስ ማደናቀፉን ቀጥሏል። ለእነዚህ ክልሎች ከተመደበው ገንዘብና ሀብት በተጨማሪ ተደራሽነቱ እንዲረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። ይህን ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው  ሲሆን የአለም አቀፉ ማህበረሰብም የሚያተኩርበትና የሚከታተለው ነው።

ኢትዮጵያዊያን እንደመሆናችን ህዝቡ ዕርዳታ ማግኘት አለበት ብለን እናምናለን፡፡ በዋነኛነት የሚያሳስበን የህዝባችን ህልውናና ደህንነት ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ ይህ ቡድን ጥረታችንን እያደናቀፈ እና እያገደ ነው። የዕርዳታው መድረስ የሚረጋገጠው በግጭት ወደተጎዱ አካባቢዎች መሄድ ሲቻል ብቻ ነው። በተጨባጭ የሚታዩትን እውነታዎች በሙሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀቁን ግን መካድ የለብንም፡፡ አካፋን አካፋ ማለት ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ ይሄ ሀቅ በደንብ መታወቅ ብቻ ሳይሆን በጥብቅ መወገዝም  ያለበት ነው።

እንደ የዓለም የምግብ ፕሮግራም/ WFP ካሉ አለም አቀፍ አጋሮች ጋር እየሠራን ነው። ነገር ግን የአማራና የአፋር ክልሎች በሕወሃት ወረራ ክፉኛ የተጠቁ በመሆናቸው አጋሮቻችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በነዚህ ክልሎች በሚገኙ መዳረሻዎች ላይ የሚደረገውን የዕርዳታ አቅርቦት የበለጠ ትኩረት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። ምንም እንኳን በዕርዳታ መገኘትና እና በአቅርቦት ላይ አንዳንድ ክፍተቶች ባይታጡም፣ በተጨባጭ ባለው አስቸኳይ ፍላጎት እና አሁን እየተደረጉ ባሉት ጥረቶች መካከል የጎላ ክፍተት ይታያል።

እንደኔ ግምት በሱዳን ውስጥ የነበረውን ሁኔታ በማጤን አልበሽርን በጽኑ የደገፈ አገዛዝን በመቃወም የነበረውን መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ሁኔታ ለመረዳት በዚያን ጊዜ በሱዳን የነበረውን ሁኔታ አጽንዖት መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በነጻነትና በለውጥ ኃይሎች የሚመራው በሕዝባዊ ንቅናቄ ከስልጣናቸው እንዲለቁ በመጠየቅ ከፍተኛ ተቃውሞ አድርገዋል። ተቃውሞው በዋና ከተማይቱ ካርቱም ብቻ ሳያበቃ ኤፕሪል 11 ቀን 2019 እ.ኤ.አ ከስልጣን እስኪወገድ ድረስ ሰልፎቹ ከዲሴምበር 2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ ተቀባይነት አግኝተዋል።

የሱዳንን ስልጣን ለሶስት አስርት አመታት ተቆጣጥሮት የነበረውን ወታደራዊ ተቋም አልበሽር ሙሉ ኃይሉንና ስልጣኑን ተረክቧል። በዚህም የኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ሚና በሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች መካከል የስልጣን ክፍፍል ስምምነትን መፍጠር ነበር ይህም ተጨማሪ ደም እንዳይፈስና ሱዳን ማለቂያ ወደሌለው የደም መፋሰስ እንዲሁም ወደ ስርዓት አልበኝነት አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ ማድረግ ነበር።

ኢትዮጵያ በሱዳን ያለውን ትርምስ ለማስቆምና ሰላምን ለማስፈን የተሳተፈችበት ምክንያት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያላት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ነው። ምንም እንኳን በሚያሳዝን ሁኔታ ላጭር ጊዜ ቢሆንም ተሳክቷል ብዬ አምናለሁ።

ሱዳን በአልበሽር መሪነት “ብሄራዊ ውይይት” ሞክረው ነበር ነገር ግን ባለመስማማት ተጠናቀቀ። የልሂቃን መግባባት እየተባለ የሚጠራው ጉዳይ በመጨረሻ የሥልጣን መጋራት ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም።

ሆርን ሪቪው:

ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን አደራዳሪነት እኩል ተቀብለውታል?

ጊዜውን መለስ ብለን ስንመለከት የሱዳን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ካለፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ ሁለቱም ወገኖች ሚናችንን በአዎንታዊ መልኩ ተቀብለውታል። ከሁሉም በላይ ግን የሱዳን ሕዝብ ኢትዮጵያ ረድታናለች ብለው ያምናሉ።

ሆርን ሪቪው፡-

ሱዳን አሁን ላለችበት አሉታዊ ችግር ያደረሷትን አንኳር ጉዳዮች እንዴት ያዩታል?

ሱዳን እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በአሉታዊ የታሪክ ቁርሾ ተጎጂ ነች። የሱዳንን የስልጣን ተዋረድ ስንመለከት ብዙ መፈንቅለ መንግስት ተካሂዶባታል፤ ይህ በራሱ የፖለቲካና የባህላቸውን ውስብስብነት ያሳያል። ስለዚህ የሥልጣን ጉዳይ በዴሞክራሲያዊ መንገድና ዲሞክራሲን በሚያንጸባርቅ መልኩ መስተካከል ያለበት አንድ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ሱዳን ብቸኛ ችግሯ ይህ ብቻ አይደለም አሁንም በዙሪያዋ እንዲሁም በማዕከሏ ሌሎች በርካታ ወሳኝ ጉዳዮች ያመሳቅሏታል። በአሁኑ ጊዜ ሥልጣኑ በሕዝብ እጅ ባለመሆኑ ሥልጣኑ በሕዝቡ እጅ እንዲሆን ይታገላሉ።

ሆርን ሪቪው፡-

ወቅታዊውን የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት እንዴት ይገልጹታል? የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ከሱዳን በኩል የአቋም ለውጥ ይኖራል ብሎ ይገምታል?

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የረጅም ጊዜ የጋራ መደጋገፍ ታሪክ አላቸው።

በቅርቡ፣ የኛ ጠቅላይ ሚኒስትር በፖለቲካ ልሂቃን እርቅ እና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምስረታ ላይ በጥረታቸው ያሳኩትን እናስታውሳለን፡፡ በተመሳሳይ ኢትዮጵያውያን ችግር ሲገጥማቸው ከሱዳን ጎረቤቶቻቸው ልባዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ይህ የሱዳን አመራር በውጫዊ ሁኔታዎችም ሆነ በተጽእኖ አምጪ አካላት ምክንያት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት የደፈረበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡  ለዚህ ጉዳይ ኢትዮጵያ አፋጣኝ እልባት ለመስጠት በነባር ቀጠናዊ ዘዴዎች ማለትም በኢጋድ አማካኝነት ትቀጥላለች።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በሚመለከት ህዝቦቻችን በጋራ በመሥራት ብዙ መማርና ተጠቃሚ መሆን አለባቸው። ለዚህም ነው በአሁኑ ወታደራዊ ገዥዎች የተፈጠረው ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት ያለፈ ታሪካችንን ያላገናዘበ እና ወደፊት ልናጎለብተው የምንችለውን አቅም አይመጥንም የምንለው፡፡

ሆርን ሪቪው፡

በእርስዎ እይታ በተለይም እንደ ሸምጋይነት ሂደቱን የሚያበላሹ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ?

አስተያየት የለኝም። በዚህ ጉዳይ ዝምታን እመርጣለሁ። ሆኖም ወደፊት በሰፊው የምገልጸው ይሆናል።

ሆርን ሪቪው፡

አሁን ሱዳን ባለችበት የመልካም አስተዳደር ችግር ወደፊት በምን አይነት መልኩ መቀጠል ይችላሉ ብለው ያምናሉ?

በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የተሻለች ሱዳን እንድትኖር የሚተጉ ፣ ነጻነትን ፣ ፍትሕንና ሰላምን እውን የሚያደርጉ ፣ ምሁራንና ወጣቶችን (ወንዶችም ሆኑ ሴቶች) ሱዳን ማግኘት አለባት።

ሆርን ሪቪው፡

ብዙዎች በሱዳን ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት ለመፍታት ብሔራዊ ውይይት መደረግ እንዳለበት ይጠቁማሉ። እርሶ ይህንን እሳቦት መፍትሄ ይሆናል ብለው ያምኑበታል? ይህ ካልሆነ ሱዳን ወደፊት ያላት አማራጭ ምንድነው?

ሱዳን በአልበሽር መሪነት “ብሄራዊ ውይይት” ሞክረው ነበር ነገር ግን ባለመስማማት ተጠናቀቀ። “የልሂቃን መግባባት” እየተባለ የሚጠራው ጉዳይ በመጨረሻ “የሥልጣን መጋራት” ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ሙከራዎች ለሱዳን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ገና ናቸው። እንደ እኔ እምነት ሱዳን ምንም አይነት “ደሞክራሲያዊ ተመክሮና መፍትሄዎች ” ከውጭ አትፈልግም። ይልቁንም ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ መፍትሔ ከውስጥ መምጣት አለበት።

ሆርን ሪቪው፡

የሱዳን የፖለቲካ ልሂቃን ብሔራዊ ውይይት ለማድረግ የተሻለ አቋም ላይ ናቸው ብለው ያምናሉ?

ለሱዳን ሕዝብ ትልቅ ክብር ስላለኝ ይህንን ጥያቄ መመለስ ያለበት በእኔ ሳይሆን በሱዳን ሕዝብ ነው ብዬ አምናለሁ፤

Share