በአገሮች መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስናሰላስል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ኮምፓስ መቆጣጠር የሚቻልባቸው መንገዶች ማኅበራዊና ሕዝባዊ ግንኙነቶች መሆናቸውን ብዙ ጊዜ እናስተውላለን። ምንም እንኳን ዲፕሎማሲ የሀገራት መመዘኛ እና መልካም ስም መለኪያ ቢሆንም በዋናነት ህዝቦች ትክክለኛ ሚዛን እና ተቆጣጣሪ ተደርገው ይወሰዳሉ። ዲፕሎማሲ የተለያዩ ፅንሰ- ሀሳቦች ሲኖሩት አንዳንዶቹ ኦፊሴላዊ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ህዝባዊ ናቸው ዛሬ የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የሱዳን የሶስትዮሽ ግንኙነቶችን ለማንሳት እንሞክራለን።
ሦስቱ አገሮች በየደረጃው እያዩዋቸው ካሉት ለውጦች አንፃር በመካከላቸው ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ኋላ መለስ ብሎ፣ ገለልተኛ በመሆን ጥልቅ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ማሰላሰል ይጠይቃል። በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ጎረቤት የሆኑት ሶስቱ ሀገራት የተለያዩ ግንኙነቶች እንዲኖራቸው አድርጓል እነዚህም ግንኙነቶች በዲፕሎማሲ ክትትል እና ጥበቃ ስር ይተዳደራሉ። ይህ በመካከላቸው ያለው ጉርብትና በሶስቱ ሀገራት ላይ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ ተፅዕኖ ሊያሳድር ችሏል።
እነዚህ ሀገራት ሆን ብለውም ይሁን ባለማወቅ የእር በርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና ለማሻሻል ብለው በሚያደርጓቸው ጥረቶች የሚጠብቁትን ውጤት ላያገኙ ይችላሉ! ቁም ነገሩ እነዚህ ውጤቶች ለምን ሆኑ ሳይሆን የዚህ ሁሉ ጥረት ዋና አላማ ጥሩ ውጤት በመጠበቅ እንደሆነ ማወቅ ነው ብየ አምናለሁ። በሰው ልጆች መካከል ያለው ልዩነት ተፈጥሮአዊ ነገር ነው። አለማችን በውስጧ ባሉ ነገሮች መካከል ልዩነቶች አሉ ስለዚህም የተለያዩ ቅርጾች፣ ቀለሞች፣ ሀሳቦች፣ እምነቶች፣ ወዘተ… ይገኙባታል። ልዩነታኝንን ለአለማችን እንደተሰጠ ስጦታ አድርገን ስናየው እና ሁሉም ከስጦታው የድርሻውን የወሰደ መሆኑን ስንገነዘብ ውበት ይሆናል።
እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ያለው ልዩነት ወደ እውነተኛ አለመግባባት ተቀይሯል ወይንስ አሁንም ለሦስቱ አገሮች በሚስማማ መልኩ መቆጣጠር የሚቻል ነው? ዋናው ችግር አለመግባባታችን እንጂ ልዩነታችን እንዳልሆነ ይታወቃል። ምናልባት በእነዚህ አገሮች መካከል ያለውን ታሪካዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ለመተረክ ግዜ ባይኖረንም ሦስቱን ሕዝቦች በሁሉም መስክ ከሚያቀራርቡ ትስስሮች መካከር የተወሰነ ልንወስድ እንችላለን።
እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ያለው ልዩነት ወደ እውነተኛ አለመግባባት ተቀይሯል
ወይንስ አሁንም ለሦስቱ አገሮች በሚስማማ መልኩ መቆጣጠር የሚቻል ነው?

እናም የእነዚህን ሀገራት ማህበራዊ ትስስር ስናሰላስል የጋራ ትስስር አጠቃላይ እይታ እንዲሁም በመካከላቸው ያለው የዲፕሎማሲያዊ ወይም ሌላ ግንኙነቶች ተፅእኖ ምክንያቶችን መለየት እንችላለን። በሶስቱ ህዝቦች መካከል ያለው ማህበራዊ፣ ሕዝባዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ግንኙነቶች ምን እንደሚመስሉ ለታዛቢዎች የተደበቀ አይደለም፣ ምንም እንኳን በብዙ ጉዳዮች ላይ ውጥረት የበዛበት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቢኖርም ፣ይህም በበርካታ የጋራ ማህደሮች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት መሆኑን ደርሰንበታል።
ሆኖም የአንዳንድ ጉዳዮች ክምችት ይህን አለመግባባት በአስደንጋጭ መልኩ እንዲያድግ ቢያደርግም እና የተወሰነ ተፅኖ ቢኖረውም በሶስቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ካለው ጠንካራ ግንኙነት እና ህዝባዊ ትስስር አንፃር ደካማ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም።
የሶስቱ ሀገራት ዲፕሎማሲ በብዙ ለውጦች እና ፈተናዎች እንዳለፈ ታሪክ ዘግቦታል። በተለያዩ ጊዜያት ከባድ የሆኑ ችግሮች ቢኖሩም ትስስሩ የሚያደርገውን የህልውና ትግሉ ላይ ያለውን ፅናት ልናይ ችለናል።
አገራችን እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ ለረጅም ጊዜ ያለመግባባት ምንጭ ነበር ይህም ፋይል በእኛ ጊዜ የአፍሪካ ትእይንት ርዕስ ለመሆን በቅቷል:: የህዳሴው ግድብ ችግር መሰረቱ እና ውስብስብነቱ ከታሪክ ባይደበቅም ነገርግን በዚህ ፅሁፌ ላይ በልማት፣ በብልጽግና የተሞላ አዲስ ጎህ እንዲወለድ እና የተስፋ ሻማ እንድናበራ በማሰብ እንዲሁም ፍትህ፣ ሰላም እና መልካም ጉርብትና በውዷ አህጉራችን እንዲስፉፉ ካለኝ ፍላጎት አለመግባባታችንን የተረሳ ታሪክ ማድረግን መርጫለሁ። እንደ እኔ እይታ በአፍሪካ ቀንድ እየተከሰቱ ካሉት ፈጣን ክስተቶች የዚያ አካባቢ ህዝቦች ህጋዊ ምኞታቸውንና አላማቸውን የሚያሟላ ብሩህ የወደፊት ተስፋ እንዳላቸው እርግጠኛ ነኝ።
በነዚህ ትልቅ ምኞቶች መጠን ተግዳሮቶቹ እየበዙ መጥተዋል። የታላቁ የሀበሻ ሕዝብ ምን ያህል ብዙ ችግሮችን እንዳሳለፈ ታሪክ ቢዘግብም ነገር ግን ባጠቃላይ የኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካውያንን ለውጥ እና እድገት ሊፈጥር ችሏል። አንዳንድ ጎረቤት አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር ለረጂም ግዜ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የሰለጠነ እና መልካም የሆነ ግንኙነት መፍጠር እየቻሉ ኢፍትሐዊ ታሪክ በመጠቀም ፖሊሲያቸውንና እድገታቸውን ኢትዮጵያን ወደኋላ በማስቀረት ላይ የተመሰረት አድርገዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን አንዳንዶች በተለያየ መንገዶች ለማደናቀፍ እና ለማስቆም ብዙ ጥረቶኝ ቢያደርጉም ነገር ግን ይህን የኢትዮጵያ አገራዊ ህዳሴ ጉዞ ለመቀጠል የተነሳ ቆራጥ መሪ እንዳለን የዘመናችን ታሪክ አስፍኖታል። ይህም መሪ የኖቤል የሰላም ሽልማት ባለቤት የሆኑት ክቡር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ናቸው። ምናልባት አንዳንዶች ይህ ሽልማት የተሰጠውን ሰላም በማስጠበቅ ስም የኢትዮጵያን መብት አሳልፎ እንዲሰጥ ነው ብለው ያምኑ ነበር።
እንዲሁም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ክብርና ህጋዊ ህዳሴ ለመናድ ነው ብለው ያስቡ ነበር!
አንዳንዶችም የውጭ አካላትን አጀንዳዎች ለማሳካት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እና የህዝቡን ፍላጎት ለመቆጣጠር በሽልማቱ ጫና ለማድረግ ያስቡ ነበር።
ኢትዮጵያን ፊት ለፊት የመጋፈጥ ሞራል እና ድፍረት እንደሌላቸው ስለሚያውቁ ተላላኪዎችን እና ከጠባብ ጥቅሞቻቸው ጀርባ የሚሹ የሀገርንና የመብት ጥቅምን ቅንጣት ታክል ግምት የማይሰጡ አካላትን እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
ነገር ግን እንደ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ፍልስፍና ለዚህ ክብር ሽልማት ተገቢ ባለቤት ለመሆን እውነተኛ ሰላም ያስፈልጋል። ያንን ሰላም፣ ፍትህና ሁለንተናዊ እድገት ለማስመዝገብ ፅናትንና ቁርጠኝነትን መጠቀም አጥብቆ ይጠይቃል! ስለዚህም የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የኢትዮጵያ አገራዊ ጉዞ የጀመረው ከአቻቸው የተከበሩ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ፈገግ ብለው ባቀረቡት ከባድ የሆነ ቃለ መሃላ የመፈፀም ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ነው።
ይህ የሆነበት ምክንያት የግብፅና የሱዳን ወንድሞች ከጠየቁት አስገዳጅ ስምምነት በላይ በፈጣሪ ስም ቃል ኪዳን መግባት የበለጠ ከባድ እና አስገዳጅ ነው ተብሎ ይታመናል።
አሁንም አገራችንና አመራራችን ከወንድሞቻችን ጋር ያለጥፋትና ጉዳት እንዲሁም ያለቸልተኝነትና ያለማጋነን በመልካም ዓላማና ጉርብትና መስራትን አደራ እንላለን።
እናም በዚህ ቃለ መሃላ ይዘት ላይ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሕሊና ውስጥ ከተመሠረተው መተማመን እንዲሁም ለግብፅ ወንድሞች ካላቸው እምነት እና በጎ አስተሳሰብ ያለምንም ማመንታት እና በሙሉ እርግጠኝነት መሐላ መስጠቱ ምንም አልከበዳቸውም። የግብፅ ፕሬዝደንት እና ታዳሚው የተደሰቱበት ቃለ መሃላ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግራቸውን በሰላምታ እና ለሁሉም ተሰብሳቢዎች መልካም ምኞት የተመኙበት እንዲሁም መልካም ጉርብትና እንደሚቀጥሉ እና በግብፅ ላይ ምንም አይነት ጉዳት ለማድረስ ፍላጎት አለመኖሩን ያካተተ ነበር።
ይህ ብቻ አይደለም ክቡር የግብፅ ፕሬዝዳንት ማንንም ሳይጠይቁ ቃለ መሃላ ለመፈጸም ያላቸውን ተነሳሽነታቸውን በመግለጽ እንዲሁም ለመተባበርና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት ቃል ገብተው ለኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ እናንተም ከግብፆችም መልካምን ነገር ያያሉ በፈጣሪ እምላለሁ፣ በፈጣሪ እምላለሁ፣ መቸም አንጎዳችሁም በማለት ንግግራቸውን ጨረሱ::
የዚያን ጊዜ ህዝቦች ለአስርት አመታት ውስብስብ ሆኖ የቆየውን የተራዘመ ቀውስ በተመለከተ ከዚህ ግንዛቤ በኋላ እፎይ ብለው ተነፈሱ::
የሁለቱ መሪዎች ቃለ መሃላ ምንም አይነት ትንተና ሳንተነትን፣ ቀውሱ በጉዳዩ ላይ የጣለው ነገር ከጊዜ በኋላ ለሁላችንም የሚያረጋግጠው ነገር በሀገራችን ላይ በድብቅም ሆነ በአደባባይ የተነደፉት አጀንዳዎች አንዳንዶች በጊዜያዊነት ከሚያሳዩት መልካም ስነ ምግባር እጅግ ያለፈ እንደሆነ እና ሌላ ጥቁር ድብቅ ዓላማዎችን ለማሳካት እንደሚጠቀሙበት ልናይ ችለናል:: አሁን የጠቀስናቸው አካላት የኢትዮጵያን አንድነት፣ መረጋጋትና ብልፅግና እንደግፋለን እያሉ ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ በውስጥ ጉዳዮቿ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እና የማዳከም እንዲሁም ቀጠናውን ለማራበሽ ኢትዮጵያን መከፋፈል ዓላማ በማድረግ ማዕቀብ የሚጥሉ ናቸው::
በሱዳን ያሉ ወንድሞቻችን ለሶስቱ ህዝቦችና ለመንግስቶቻቸው መልካም ነገር ከማያስቡ ሁለት ፊት ካላቸው የተለያዩ አካላት ላይ ያላቸው አቋም ፅኑ እና ግልፅ አልነበረም:: ኢትዮጵያ በወንድም ሀገር ሱዳን ውስጥ በወቅቱ ሀገሪቱን በወረረ ግጭት ሰላም ፈጣሪ ነበረች። አገራችን አንዳንድ የሱዳን ግለሰቦች በያዙት ተቀያያሪ አቋም ላይ ምንም ትኩረት አልሰጠችም ነበር። የአቋሞቻቸው መጋጨት የሚያሳየው እነዚህ አመለካከቶች በስነምግባር ኬላ ሳያልፍ ሆን ተብሎ ወደ ሱዳን የገባ እንደሆነ ምንም ጥርጥር እንደሌለው ያረጋግጣል።
አሁንም በሶስቱ ህዝቦች መካከል በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ በተመሰረተ በጋራ ትብብር፣ በሶስቱ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት ሳይኖር እንዲሁም እነዚያን ህዝቦችን ለሚወክሉ ሚድያዎች ተገቢውን ክትትል በማድረግ በጠንካራ መሰረት ላይ እንደገና በማጤን እና በመገምገም ግንኙነታቸውን ለማሻሻል እድሉ አለ።
ይህንንና ሌሎች በቀጠናው ውስጥ ያሉ ቀውሶችን ለመፍታት የተተወው የድርድር ጠረጴዛ ቁልፍ ይሆናል ብለን እናምናለን። በመጠባበቅ ላይ ያለው የህዳሴ ግድብ ድርድር ፈታኝ እየሆነ

መጥቷል ይህም በብዙ ምክንያቶች የተወከለው ነው። በተለይም፡-
- የሚቲወቁም ሆነ የማይታወቁ አካላት በህዝቦች መካከል በፈጠሩት ግጭት
- የአመለካከቶች እና የአቋሞች ለውጥ
- የሌላውን ተደራዳሪ አካል አቋም ግምት ውስጥ ያላስገቡ ጥያቄዎች መጠየቅ
- በተደራዳሪዎች ላይ የውሸት ቅድመ-ግምቶች እና የተሳሳቱ ትርጓሜዎች እና ትንታኔዎች መስጠት
- ዓላማዎች አስቀድመው ሳይወስኑ ድርድሩ ላይ ግትር መሆን
- ሚዲያዎችን እና ዲፕሎማሲዎችን አሉታዊ እና አሳፋሪ በሆነ መንገድ በመጠቀም ድርድሩን ለማበላሸት እና በድርድሩ ላይ ባሉ ወገኖች ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከር ናቸው።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ በግብፅ እና በሱዳን ወንድሞቿ ላይ ያላትን በጎ አመለካከት ለአለም እያሳየች እና እያስመሰከረች ያለች ሲሆን፤ ለችግሩ መፍትሄ በመፈለግ ረገድ ድሮም ሆነ አሁን እያደረገችው ያለ እንቅስቃሴ በፍትህ አይን ለሚያይ ግልፅ ነዉ። በዚህ ረገድ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የበላይ አመራሮች ከችግር ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሰጡትን መግለጫዎች መመልከት ይችላሉ። ከዚያም በኋላ ተፉሰስ ሀገራት መግለጫዎች ጋር በማነፃፀር ብዙ ነገር መረዳት ይቻላል። አሁንም አገራችንና አመራራችን ከወንድሞቻችን ጋር ያለጥፋትና ጉዳት እንዲሁም ያለቸልተኝነትና ያለማጋነን በመልካም ዓላማና ጉርብትና መስራትን አደራ እንላለን። ቁም ነገሩ ቀውሶቻችንን መሻገሪያ መንገድ አድርገን ወደፊት መራመድ እንጅ አንድኛችን አንድኛችን ላይ አሸናፊ መሆኑ አይደለም።