ይህ ርዕስ በህዳሴው ግድብ ጀርባ ካለው በቢልዮን ከሚቆጠረው ውሀ ሊበልጥ የሚችል ዝርዝሮች የያዘ ርዕስ ነው ማለት ይቻላል! በህዳሴው ግድብ ላይ እውቀት ያላቸው ፍትሃዊ ባለሞያዎች ይህ ርዕስ ልክ በሱዳንና በግብፅ ወንድሞቻችን ላይ እደሚዘንበው ዝናብ አስፈላጊ መሆኑን በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።

ሳይንሳዊና ቴክኒካል ትንተናዎች ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራትና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችው ቃል ማረጋገጥ ካልቻሉ በቴሌቭዥን እና በተለያዩ ሚድያዎች ከመታየት ውጭ ምንም ነገር አላበረከቱም ማለት ይቻላል።

እሁን ለአስርት አመታት አልፎ ተርፎም ለዘመናት አብረን የተጓዝንበት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነን። ያለፉት ዓመታት ያጋጠሙን ችግሮች ሁሉ ምንም እንኳን ባያስታውቀንም ይበልጥ እንድንቀራረብ አድርጎናል።

እናም በማንኛውም መልኩ የአንዱ የጠይሟ አህጉራችን ክፍል ድል ቢያገኝ፣ ደስታው ሌሎቹን የአህጉሪቱ ክፍሎች ሁሉ ያዳርሳል።

የበላይ መሪ የሆነች ትልቅ ተስፋ ያላት አህጉር አለችን …

አፍሪካ… የአለም ገነት…

ታዲያ ያለ ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን የምንኮራበት አፍሪካ ልትኖር ትችላለችን??

የሰላም መርከቦች በአቢሲኒያ ከፍታዎች በጥቁር አባይ ዳርቻ ላይ አርፈው ኢትዮጵያዊያን ከግብፅና ከሱዳን ጋር ውህደት፣ ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።

እኔ እዚህ የእነዚህን ስማቸው ብቻ የሚበቃ ሶስት ሀገራት ታሪካዊ ታላቅነት ለመዘርዘር አይደለም የቀረብኩት። በጌታ ፈቃድ ሦስተኛው ሙሌት ከተጠናቀቀ በኋላ አድማሱ ተከፍቶ ከመጣላት እና ካለመግባባት ይልቅ ትብብር እና አንድነት ከረጅም ጊዜ በፊት መጀመር እንደነበረብን ግልፅ ያደርግልናል። እነዚህ የብልጽግና እና የዘላቂ ልማት ሰንደቅ ዓላማዎች የሚውለበለቡባቸው አድማሶች ናቸው።

ከሦስተኛው ሙሌት በኋላ፣ አሁንም ያልተስማማንባቸውን ነጥቦች መከለስ ይጠበቅብናል። የህዳሴ ግድቡ አስከፊ አደጋ ነው እያለ ጉዳቱን ሲጠብቅ የነበረ አሁን በተጨባጭ የህዳሴውን ግድብ ጥቅምና አዋጭነት መዳሰስ ችሏል!

እንዲሁም የህዳሴው ግድቡ ካለቀ በኋላ ጥማትን እና ሞትን ሲጠብቅ የነበረ ሁሉ። በአላህ ፈቃድ ዉሀው ኤሌክትሪክ ካመረተ በኋላ የህዳሴው ግድብ በሮች ዉሀው በአግባቡ እንዲደርሳቸው አድርጎ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ በኤሌክትሪክም በውሀም ማስደመም ችሏል።

የክፋት መንገዶች ይፈርሳሉ የመልካምነት መንገዶች ጸንተው ይቆያሉ። ስለዚህ በግብፅ እና በሱዳን ያላችሁ ወንድሞች ለሀገራችንና ህዝቦቻችን ወደሚጠቅም ትብብር እንድትመጡ ጥሪ አቀርባለሁ። ያለፈውን አልፈን አሁን ያለውን በጋራ እንገንባ።

የአገሮቻቸውን ጥቅም ከግለሰቦች ጥቅም በላይ የሚያሳስባቸው አገሮች እንዴት ልዩ ናቸው? እስኪ ጮክ ብለን እንበል፡- የህዳሴው ግድብ የሚያስተሳስረን ፕሮጀክት ነው።

Share